logo

በእርግዝና ወቅት የተለመዱ ችግሮች

ከፍተኛ የቅሪት ትዉከት

ከፍተኛ የቅሪት ትዉከት Hyperemesis Gravidarum ምንድን ነዉ? ከፍተኛ የቅሪት ትዉከት ማለት በእርግዝና የመጀመሪያ 20 ሳምንታት የሚከሰት ከመጠን ያለፈ የማቅለሽለሽ እና ማስመለስ በሽታ ነው። በእርግዝና ወቅት እስከ 16 ወይም 18 ሳምንታት በአብዛኛው ነፍሰጡር እናቶች ላይ ይህ ስሜት ቢኖርም ከፍተኛ የቅሪት ትዉከት ግን እስከ 2% የሚሆኑ ነፍሰጡሮችን ያጠቃል። ከፍተኛ የቅሪት ትዉከት ምልክቶች፣

ምክንያት

በአብዛኛው አይታወቅም ነገር ግን የእርግዝና ሆርሞን ማለትም HCG እና Estrogen መጨመር ጋር በተያያዘ፣ከአንድ በላይ ፅንስ እርግዝና፣ያልተለመደ የእንግዴ ልጅ  የእርግዝና አይነት፣ ከዚ በፊት የነበረ የመኪና ጉዞ ህመም Motion sickness ፣  የቤተሰብ ተመሳሳይ ህመም ታሪክ፣ በቀድሞ እርግዝና ተመሳሳይ ህመም መኖር እና የመሳሰሉት።

ምልክት

ሕክምና

ወደ ሐኪም

ድንገተኛ የፅንስ መቋረጥ

ድንገተኛ የፅንስ መቋረጥ የምንለው ፅንስ ከተፈጠረ ከ 28 ሳምንታት በፊት የሚከሰት ድንገተኛ ውርጃ ነው።ይህም ከአጠቃላይ እርጉዝ እናቶች ዉስጥ 30% የሚሆኑት ላይ የሚከሰት ክስተት ነው።

ምክንያት

ምልክት

ሕክምና

መከላከል

ወደ ሐኪም

የእርግዝና ወቅት ስኳር

የእርግዝና ወቅት ስኳር በእርግዝና ሰዓት የሚከሰት የስኳር አይነት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በእርግዝና ወቅት የምርመራ የሚገኝ ነው። ስኳር በአራት ዋናዋና አይነቶች ያሉት ሲሆን የእርግዝና ወቅት ስኳር አራተኛው አይነት ስኳር በመባል ይታወቃል።

ምክንያት

ምልክት

ሕክምና

መከላከል

ወደ ሐኪም

የእርግዝና ወቅት ግፊት

የእርግዝና ወቅት ግፊት ማለት፣ በእርግዝና ጊዜ በሚከሰት ከፍተኛ የደም ግፊት የተነሳ አንዳንድ ጊዜ በሰውነት ውስጥ የውሀ መጠራቀም እና በሽንት ውስጥ ፕሮቲን ሲኖር ይህም ከ20 ሳምንት ጀምሮ እሰከ ወሊድ ብሎም ስድስት ሳምንት የሚደርስ የግፊት አይነት ነው።

ምክንያት

ምልክት

ሕክምና

መከላከል

ወደ ሐኪም

የድህረ ወሊድ ደም መፍሰስ

በምጥ ለወለደች እናት >500ሚሊ ፥በቀዶ ህክምና ለወለደች >1000ሚሊ እንዲሁም መንታ እርግዝና ከነበረ >1500ሚሊ በላይ ደም ከፈሰሳት ነው።ምን ያህል እንደደማች በትክክል ማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ ሌሎች ምልክቶችን ማስተዋል ያስፈልጋል።

ምክንያት

አጋላጭ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?

አንዲት እናት ከፍተኛ የደም መፍሰስ ሲያጋጥማት ምን ማድረግ አለብን?

መከላከል

ወደ ሐኪም

ስለ ድህረ ወሊድ ጭንቀት፥ድባቴ እና ሳይኮሲስ

የድህረ ወሊድ ጭንቀት ወይም የሃዘን ስሜት በመጀመርያዎቹ የወሊድ ሳምንታት በብዙ እናቶች ላይ የሚከሰት ችግር ሲሆን በሆርሞን መዛባትና የኑሮ ለውጥ ምክንያት የሚመጣ ነው። ከምልክቶቹም መካከል የሃዘን ስሜት፥መነጫነጭ፥የስሜት መለዋወጥ፥ማልቀስ ጥቂቶቹ ሲሆኑ ቀላልና እስከ 2 ሳምንት ባለው ጊዜ በራሱ የሚስተካከል (self limiting)ነው።

የድህረ ወሊድ ድባቴ

በመጀመሪያዎቹ የወሊድ ወራት ላይ የሚከሰት የአእምሮ ጤና ችግር ሲሆን ከወሊድ በኋላ የሚኖሩ የሆርሞን እና የሰውነት ለውጦች ከሌሎች የአእምሮ እና ማህበራዊ ጫናዎች ጋር አንድ ላይ በመሆን ከወሊድ በኋላ የሚከሰት ድባቴ (Postpartum Depression) ሊያመጡ ይችላሉ። ከ 10-15% የሚሆኑ እናቶች ከወሊድ በኋላ የድባቴ (depression) ተጠቂ ናቸው።

ምልክት

የድህረ ወሊድ ሳይኮሲስ

ከወሊድ በኋላ አልፎ አልፎ የሚከሰት(rare) ነገር ግን ከፍተኛ የአእምሮ ጤና ችግር

ምልክት

ወደ ሐኪም