logo

የእርግዝና ሂደት

የመጀመሪያ ሶስት ወር
  • 3ኛ ሳምንት ፅንሰት የሚፈጠርበት ነው
  • 4ኛ ሳምንት የተፈጠረው ፅንስ ወደ ማህፀን ግድግዳ ውስጥ ማደግ የሚጀምርበት
  • 5ኛ ሳምንት የልብ መምታት የሽንት እና መራቢያ ኡደት አካላት፥የኩላሊት መፈጠር
  • 9ኛ ሳምንት የፅንሱ መጠን 3/4ኢንች
  • 11ኛ ሳምንት የፅንሱ የመራቢያ አካላት መታወቅ ይችላል።
  • 12ኛ ሳምንት የእጅ ጥፍር መታየት እና መጠኑም 14 ግራም ይደርሳል።
ሁለተኛው ሶስት ወር
  • የፅንስ እድገት
  • 13ኛ ሳምንት የ አጥንት መጠንከር
  • 14ኛ ሳምንት የቀይ የደም ሴል መመረት ወደ 45 ግራም ይመዝናል
  • 15ኛ ሳምንት የአናት ፀጉር መታየት
  • 16ኛ የፅንስ አይን ቦታዉን መያዝ ይጀምራል
  • 17ኛ ሳምንት የእግር ጥፍር መታየት
  • 18ኛ ሳምንት ፅንሱ ድምፅ መስማት ይጀምራል፥የምግብ ኡደት ይጀምራል
  • 19ኛ ሳምንት ሴቶች የማህፀን እና መራቢያ አካል እድገት
  • 20ኛ ሳምንት የመጀመሪያው የፅንስ እንቅስቃሴ፥ወደ 320ግራም አካባቢ ይመዝናል።
  • 21ኛ ሳምንት ፅንስ ጣቱን ወደ አፍ ይይዛል
  • 23ኛ ሳምንት የአይን እንቅስቃሴ መጨመር
  • 24ኛ ሳምንት የደም ስሮች ሲታዩ የቆዳ ቀለም ወደ ቀይ መቀየር
  • 27ኛ የሳንባ እድገት መጨመር
ሶስተኛው ሶስት ወር
  • 28ኛ ሳምንት የፅንሱ አይን በትንሹ መከፈትና የሳንባ እንቅስቅሴ
  • 29ኛ ሳምንት ከፍተኛ የፅንስ እንቅስቃሴ፡ እጅና እግር መለጠጥ
  • 30ኛ ሳምንት የፅንሱ ፀጉር ማደግ
  • 31ኛ ሳምንት የፅንስ ክብደት በፍጥነት መጨመር
  • 32ኛ ሳምንት የመተንፈስ እንቅስቃሴ መጨመር
  • 33ኛ ሳምንት ፅንሱ ብርሃን ማወቅ ይችላል፣
  • 34ኛ ሳምንት የፅንሱ ጥፍሮች ያድጋሉ፣
  • 35ኛ ሳምንት የቆዳው መለስለስ ስብ መከማቸት
  • 36ኛ ሳምንት ጭንቅላት ወደ ታች መገልበጥ
  • 38ኛ 39ኛ ሳምንት ከ 2900ግራም በአማካይ በላይ ይመዝናል፣
  • ደረቱ መታየት፣የወንድ የዘር ፍሬ ቦታዉን መያዝ ፣የመውለጃ ጊዜ መቃረብ።

የተለመዱ ችግሮች

ኧርብስ ፓልሲ

ኧርብስ ፓልሲ በ አንድ እጅ ላይ የሚከሰት የመድከም ወይም አጅን መጠቀም አለመቻል ነው።

ምልክቶቹ

  • እጅን ማንቀሳቀስ አለመቻል
  • የእጅ ወደኋላ መዞር
  • የእጅ መዝለፍለፍ እና የክንድ ጡንቻወች መጠን መቀነስ
  • በእጅ ላይ የስሜት ህዋሳትንእና ጥንካሬ ማጣት የመሳሰሉት

ሕክምናዎች

  • በተከታታይ በሚሰጥ የፊዚዮቴራፒ ህክምና
  • በቀዶ ህክምና አማራጭ
የህፃናት ቆልማማ እግር

ቆልማማ እግር ህፃናት ሲወለዱ ጀምሮ በአብዛኛው በሁለት እግር የሚታይ የእግር መጣመም ነው።

ምልክቶቹ

  • የእግር ወደ ውስጥ መዞር
  • የባት እና እግር በመጠን መቀነስ
  • ያልተለመደ የቆዳ እጥፋት መኖር

ሕክምናዎች

  • በጀሶ የሚደረግ ህክምና
  • የጅማት ቀዶ ጥገና
  • በጫማ የህክምና አማራጮች አሉ
የህፃናት ቢጫነት

የአይን ቀለም እና የቆዳ ቀለም ቢጫ ቀለም ሆኖ መታየት ነው። ይህም የቢሊሩቢን የተባለው ኬሚካል መጠን ሲጨምር የሚከሰት ነው።ከ50-60% ህፃናት ላይ ይታያል።ያለ ጊዜ የተወለዱ እና የሰውነት ክብደታቸው ዝቅተኛ የሆኑ ከ2.5ኪ.ሎ በታች ጨቅላ ህፃናት ላይ በስፋት ይታያል።

ምክንያት

ምክንያት

  • የደም መቋጠር በወሊድ ጊዜ
  • የቀይ የደም ሴል መብዛት
  • የጨቅላ ህፃናት ኢንፌክሽን

ሕክምናዎች

  • የደም ቅይይር
  • ለኢንፌክሽን የሚሰጡ መድሃኒቶች
  • የሰማያዊ ብርሃን መሳሪያ ላይ በማቆየት

የጨቅላ ህጻናት አመጋገብ

የጨቅላ ህጻናት አመጋገብ (ከወሊድ እስከ 6 ወር) አዲስ የተወለዱ እስከ 6 ወር የእናት ጡት ወተት ብቻ እንዲመገቡ ይመከራል። እስከ 3 ወር ባለው በየ 2/3 ሰዐት 10-12 ጊዜ መውሰድ አለባቸው። ከ 4 ወር በላይ ለሆናቸው ጨቅላ ህጻናት በየ 4/5 ሰዐት መመገብ ይመከራል። ህጻናት ምግብ በሚያስፈልጋቸው ፣አፋቸውን መክፈት፣ ጣታቸውን መጥባት፣ ማልቅስ እና መነጫነጭ ያሳያሉ።

የበለጠ ይማሩ